by voice of fano
መንግስትን በመተቸት የሚታወቁት ታዬ ደንደአ በጠቅላይ ሚንስትሩ ከስልጣን መነሳታቸውን በፌስብክ ገፃቸው እንደሚከተለው አስታውቀዋል ----- ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የተናገሩትንና የፃፉትን የመደመር እሳቤ አምኜ ተከተልኩዎት:: አሁን ግን በተናገሩት የማይኖሩ ብቻ ሳይሆን በሰዉ ደም የሚጫወቱ አረመኔ መሆንዎን ተረድቻለሁ:: እዉነት መስሎኝ በሀገር ህልውና ስም ሲያካሄዱ የነበረዉንና ኢትዮጵያውያንን ከማገዳደል አልፎ ሀገሪቷን ያደቀቃትን ከንቱ ጦርነት ሳዳምቅልዎ በነበረበት ወቅት ሲያወድሱኝ ነበር:: ዛሬ ነገሩ ገብቶኝ የወንድማማቾች መገዳደል ይቆም ዘንድ ለሰላም በመወገኔ ከስልጣን አነሱኝ:: ለወንበርና ለመኪና በመገዛት ኦሮሞን በኦሮሞ ለማጥፋትና ኦሮሞን ከወንድሞቹ ጋር ለማጣላት የሚጫወቱትን ቁማር እያየሁ ዝም ባለማለቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ:: ስለነበረን አጭር ቆይታ አመሰግናለሁ:: እስካለሁ ድረስ ለሰላምና ለህዝቦች ወንድማማችነት የማደርገዉ ትግል ይቀጥላል!